The Women's - The Royal Women's Hospital Victoria

Amharic

ወደሴቶች እንኳን ደህና መጡ / Welcome to the Women’s

የሮያል ዎመንስ ሆስፒታል በአውስትራሊያ ውስጥ ልዩ ሆስፒታልና ታላቁ ሲሆን በማንኛውም የእድሜ ገደብና ከተለያዩ ባህሎች ለመጡ ሴቶች የጤና ይዞታን ለማሻሻል ዓላማው ይሆናል።
ሴቶችን በመወከልና የሴቶችን ጤና እንክብካቤ በማሻሻል መልኩ ላለፉት 150 ዓመታት ሲመራ ቆይቷል። የሴቶችን ልዩነት ወደ አንድነት በማምጣት፣ እየተቀየሩ ለመጡት ፍላጎቶች፣ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው፣ ለወደፊት የሚደረጉትና በሴቶችን ላይ ስለተገኙት ልምዶች ያለውን ጠቀሜታ ተረድተናል።
በየዓመቱ ከ165 ሃገሮች የመጡና 60 የተለያዩ ቋንቋዎች የሚናገሩ እንዲሁም 42 ዓይነት የሃይማኖች ልምድ ያላቸውን ሴቶች እንደምንከባከብ ነው።


ሴቶችን በተመለከተ አስተርጓሚዎች/ Interpreters @ the Women’s

ይህ ከተለያዩ ባህሎችና ቋንቋዎች ለመጡ ሴቶች ለመንከባከብ ኃላፊነት ይኖረዋል። ከሠራተኛ ጋር ግንኙነት ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ ስለዚህ በክሊኒኮችና በአገልግሎት መሰጫ ክፍሎች ላይ እየተገኙ ስለእነሱ የጤና አጠባበቅ ውሳነ አሰጣጥ ላይ ተሳትፎ ያደርጋሉ።
ይህም በጽ/ቤቱ በሚገኙትና ከውጭ በሚመጡ ከ60 ቋንቋዎች በላይ የባለሙያ አስተርጓሚዎች ይቀርባል። እነዚህም በሴቶች ጤና ቃላት አተረጓጎም ልዩ ችሎታ ያላቸውና ከሴቶች ጤና ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ማለት ሕክምና በተመለከተና የክሊኒክ ኣሠራር ጉዳይ ላይ ጥሩ ግንዛቤ ይኖራቸዋል።


አድራሻ፡
The Royal Women’s Hospital


Locked Bag 300
Grattan St & Flemington Rd, Parkville VIC 3052
ለአስተርጓሚ አገልግሎት በስልክ: (03) 8345 3054

 

 
Powered by Komodo CMS